G

የላቲን አልፋቤት
A B C D E F
G H I J K L M
N O P Q R S T
U V W X Y Z
ተጨማሪ ምልክቶች፦
Þ...

G / gላቲን አልፋቤት ሰባተኛው ፊደል ነው።

3ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. አስቀድሞ፣ የላቲን አልፋቤት ፯ኛው ፊደል Z ሆኖ ነበር። በአንዳንድ መዝግቦች ዘንድ፣ የሮሜ ኬንሶርና አምባገነን አፒዩስ ክላውዲዩስ ካይኩስ በ320 ዓክልበ. «Z»ን ስላልወደደ ከላቲን ፊደል እንደ ጣለው ይባላል።

እስከዚህም ድረስ፣ ሦስተኛው ፊደል C እንደ ድምጾቹ «ግ» ወይም «ክ» ሊወክል ቻለ። በ230 ዓክልበ. ግድም፣ አስተማሪው ስፑሪዩስ ካርቪሊዩስ ሩጋ የ«ክ» ከ«ግ» ድምጽ ለመለየት፣ «C» ትንሽ በመለውጥ አዲስ ፊደሉን «G» እንደ ፈጠረ ይባላል። ከዚህ ጀምሮ C ለ«ክ» ብቻ፣ G ለ«ግ» ብቻ ይበቃቸው ነበር። በዚህ ወቅት ፊደሎች ደግሞ እንደ ቁጥሮች ስላገለገሉ የሌሎቹን ፊደላት ቁጥሮች ለመጠብቅ አዲሱ ፊደል «G» በቀድሞው «Z» ፋንታ በመተካት በ፯ኛው ሥፍራ ተሰካ። «Z»ም ወደ ላቲኑ አልፋበት በ100 ዓም አካባቢ እንደገና ሲመለስ፣ መጨረሻውን ቦታ ወሰደ።

ከዚህም በኋላ ከ500 ዓ.ም. ግድም ጀምሮ፣ «G» ከአናባቢዎቹ «E»፣ «I» ወይም «Y» ሲቀድም፣ በአሕዛብ ዘንድ እንደ «ጅ» ይሰማ ጀመር። ስለዚህ ከሮማይስጥ በተወለዱት ቋንቋዎች እንደ ጣልኛ GE፣ GI እንደ «ጀ» «ጂ» ይሰማሉ፣ በእንግሊዝኛም ብዙ ጊዜ እንዲህ ነው። በፈረንሳይኛም GE፣ GI እንደ «ዠ» «ዢ»፣ በእስፓንኛም እንደ «ኸ» «ኺ» ይሰማሉ። ሆኖም በነዚህ ልሳናት «G» ከ «A»፣ «O» ወይም «U» በፊት ሲቀድም፣ እንደ «ጋ»፣ «ጎ»፣ «ጉ» ይሰማል።


G

Dodaje.pl - Ogłoszenia lokalne