X

የላቲን አልፋቤት
A B C D E F
G H I J K L M
N O P Q R S T
U V W X Y Z
ተጨማሪ ምልክቶች፦
Þ...

X / xላቲን አልፋቤት ሀያ አራተኛው ፊደል ነው።

ግብፅኛ
ጀድ
ቅድመ ሴማዊ
(አልተገኘም)
የፊንቄ ጽሕፈት
ሳሜክ
የግሪክ ጽሕፈት
ኤትሩስካዊ
X
ላቲን
X
R11
- Greek chi Roman X

የ«X» መነሻ ከቅድመ-ሴማዊ ጽሕፈት እንደ ሆነ ቢታስብም እስካሁን አልተገኘም። ለዚህም ምናልባት ተመሳሳይ የግብጽ ሀይሮግሊፍ ነበር። አንዳንድ ሊቃውንት የ"ዓምድ" ("ጀድ") ስዕል እንደ ነበር ይገምታል።

ቅርጹ ከዚያ በፊንቄ (ከነዓን) ሰዎች ተለማ፣ ለድምጹም /ስ/ አገለገለ።

ግሪክኛ ግን ከ«ሺን» የደረሰው «ሲግማ» ለ/ስ/ ስላገለገለ፣ ከሳሜክ የደረሰው ቅርጽ «Ξ» በምስራቃዊ ግሪክ አልፋቤት ለድምጹ /ክስ/ ይወከል ጀመር። ሌላ አዲስ ቅርጽ «Χ» በምሥራቅ ግሪክ አልፋቤት ለ/ኽ/ ወከለ፤ በምዕራባዊ ግሪክ አልፋቤት ግን ይህ ቅርጽ ለ/ክስ/ ተጠቀመ።

ኤትሩስክኛ አልፋቤት እንዲሁም በላቲን አልፋቤት የ«X» ቅርጽ እንደ /ክስ/ ሆኖ ቆየ። በእንግሊዝኛም ደግሞ አብዛኛው ጊዜ /ክስ/ ያመልክታል። በአንዳንድ ሌሎች ቋንቋዎች ግን ልዩ ልዩ ድምጾች ሊወክል ይችላል።

ግዕዝ አቡጊዳ ደግሞ «ሰ» («ሳት») የሚለው ፊደል ከሴማዊው «ሳሜክ» ስለ መጣ፣ የላቲን 'X' ዘመድ ሊባል ይችላል።


X

Dodaje.pl - Ogłoszenia lokalne